ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ግን የእስራኤልን ቤት የናቀውንና ከእኛም ጋር እንዲሞት ወደ እኛ የላከውን ሰው እንዲያይና እንዲለይና አሞናዊውን አኪዮርን ጥሩልኝ።”
ይህንም ከማድረጋችሁ በፊት የእስራኤልን ወገን የካደውን ከእኛም ጋር ይሞት ዘንድ እርሱን ወደ እኛ የላከውን እርሱ መሆኑን አይቶ ያውቅ ዘንድ አሞናዊውን አክዮርን ጥሩልኝ” አለቻቸው።