መሳፍንት 9:56 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ ስላደረሰው በደል እግዚአብሔር የእጁን ከፈለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል፣ በአባቱ ላይ ስላደረሰው በደል እግዚአብሔር የእጁን ከፈለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት አቤሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ በፈጸመው በደል እግዚአብሔር ፍዳውን ከፈለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ቤት ላይ ያደረገውን ክፋት እግዚአብሔር መለሰበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት እግዚአብሔር መለሰበት። |
አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።
እግዚአብሔር ይህን ያደረገውም፥ በሰባው የይሩበኣል ልጆች ላይ ስለ ተፈጸመው ግፍና ስለ ፈሰሰው ደማቸው፥ ወንድማቸውን አቤሜሌክና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬም ሰዎች ለመበቀል ነው።