መሳፍንት 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ዛሬ በይሩበኣልና በቤተሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና በቅንነት ከሆነ እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ዛሬ በይሩባኣልና በቤተ ሰቡ ላይ ያደረጋችሁት በእውነትና ያለ እንከን ከሆነ እናንተ በአቢሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ዛሬ ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ያደረጋችኹት በቅንነትና ተገቢ በሆነ መንገድ ከሆነ ከአቤሜሌክ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ደስ ይበለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለይሩበኣልና ለቤቱ እውነትንና ቅንነትን ዛሬ አድርጋችሁ እንደ ሆነ የተባረካችሁ ሁኑ፤ በአቤሜሌክም ደስ ይበላችሁ፤ እርሱም ደግሞ በእናንተ ደስ ይበለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ለይሩበኣልና ለቤቱ እውነትንና ቅንነትን ዛሬ አድርጋችሁ እንደ ሆነ፥ በአቤሜሌክ ደስ ይበላችሁ፥ እርሱ ደግሞ በእናንተ ደስ ይበለው፥ |
ነገር ግን እናንተ ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ዐመፃችሁ፤ ሰባ ልጆቹን በአንዲት ድንጋይ ላይ ዐረዳችሁ፤ ዘመዳችሁ ስለ ሆነም አባቴ ከባርያው የወለደውን ልጅ አቤሜሌክን በሴኬም ነዋሪዎች ላይ አነገሣችሁት።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”