መሳፍንት 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጦርነት ተዘጋጅተው የመጡት ስድስት መቶ የዳን ሰዎች በቅጥሩ በር መግቢያ ላይ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጦርነት ተዘጋጅተው የመጡት ስድስት መቶ የዳን ሰዎች በቅጥሩ በር መግቢያ ላይ ቆመው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር መሣሪያ የታጠቁት ከዳን የመጡት ስድስት መቶ ሰዎች በዚያን ጊዜ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጦር ዕቃ የታጠቁት፥ ከዳን ልጆችም የሆኑት ስድስቱ መቶ ሰዎች በደጃፉ አጠገብ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጦር ዕቃ የታጠቁት፥ ከዳን ልጆችም የሆኑት ስድስት መቶ ሰዎች በደጃፉ አጠገብ ቆመው ነበር። |
ካህኑ ለጦርነት ከተዘጋጁት ስድስት መቶ ሰዎች ጋር በቅጥሩ በር ላይ ቆሞ ሳለ፥ ምድሪቱን ለመሰለል መጥተው የነበሩትን አምስት ሰዎች ወደ ቤቱ ውስጥ በመግባት የተቀረጸውን ምስልና ኤፉዱን፥ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ።