በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፥ አዘጋጃትም፥ ደግሞም መረመራት።
በዚያ ጊዜ ጥበብን ተመለከታት፤ ገመገማትም፤ አጸናት፤ መረመራትም።
እግዚአብሔር ጥበብን ተመለከታት ገምግሞም አከበራት፤ መርምሮም አጸናት።
በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ አከበራት፥ ደግሞም መረመራት።
ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥
ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፥ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።