ኤርምያስ 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ኃያላን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስተኞቻቸው ያለ ምሕረት የሚገድሉ ኀይለኞች ጦረኞች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፈራቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ኀያላን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ ሁሉም ኃያላን ናቸው። |
ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።”