ኢሳይያስ 32:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያዩትም ሰዎች ዐይኖች አይጨፈኑም፤ የሚሰሙትም ጆሮዎች ያደምጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤ የሚሰሙም ጆሮዎች ነቅተው ያደምጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሚያዩ ሰዎች ዐይኖች አይጨፈኑም፤ ለመስማት የሚችሉ ሰዎች ጆሮዎችም ያዳምጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በሰው አይታመኑም፤ በጆሮአቸው ያዳምጣሉ እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይጨፈኑም፥ የሚሰሙትም ጆሮዎች ያደምጣሉ። |
ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ ‘ጌታን እወቅ’ ብሎ ከእንግዲህ ወዲህ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል ጌታ። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስምና።”
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።