ገላትያ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፥ ከጸጋውም ወድቃችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕግ ለመጽደቅ የምትጥሩ፣ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤ ከጸጋ ርቃችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሕግን በመጠበቅ ለመጽደቅ የምትፈልጉ ሁሉ ከክርስቶስ ተለይታችኋል፤ ከጸጋውም ርቃችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኦሪት ልትጸድቁ የምትፈልጉ እናንተ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋዉ ወድቃችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። |
እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ አስብ፤ ንስሓም ግባ፥ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሓም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።