ዘፀአት 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወይፈኑ ደም ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣትህ ትቀባዋለህ፤ የተረፈውንም ደም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ታፈስሰዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወይፈኑ ደም ወስደህ የመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣቶችህ አድርግበት፤ የቀረውንም ከመሠዊያው ሥር አፍስሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኰርማው ደም ጣትህን ነክረህ የመሠዊያውን ጒጦች ቀባ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፍስሰው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወይፈኑም ደም ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣትህ ትረጨዋለህ፤ የተረፈውንም ደም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ታፈስሰዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወይፈኑም ደም ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ በጣትህ ትረጨዋለህ፤ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ታፈስሰዋለህ። |
ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ ይሁን፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ቁመቱ ሁለት ክንድ ይሁን፤ ቀንዶቹ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ።
ከወይፈኑም ደም ወስዶ በስርየቱ መክደኛ ትይዩ በምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ እንዲሁም ከደሙ በስርየቱ መክደኛ ፊት ለፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጫል።
በመገናኛውም ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል።
ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል።
ካህኑም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው መዐዛው ያማረ ዕጣን በሚታጠንበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ የተረፈውንም የወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል።
ከኃጢአቱም መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ግድግዳ ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈውም ደም ከመሠዊያው በታች ይንጠፈጠፋል፤ እርሱ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ እንዲያስተሰርይለትም ቀደሰው።