መክብብ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቁጣ የተነሣብህ እንደሆነ ስፍራህን አትልቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የገዥ ቍጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ ስፍራህን አትልቀቅ፤ ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጸጥ ብለህ ብትታገሥ ከባድ ለሆነው በደልህ እንኳ ይቅርታ ማግኘት ስለምትችል አለቃህ በተቈጣህ ጊዜ የሥራ ቦታህን አትልቀቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትዕግሥት ታላቁን ኀጢአት ያስተሰርያልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትዕግሥት ታላቁን ኃጢአት ጸጥ ያደርጋልና የገዢ ቍጣ የተነሣብህ እንደ ሆነ ስፍራህን አትልቀቅ። |