መክብብ 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤ እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈስሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ቤቱን ከመጠገን ቸል ቢል ጣራው ይዘብጣል፤ ክዳኑም ያፈሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰዎች ስንፍናና ቦዘኔነት የቤት ጣራ ይዘብጣል፥ በእጆች ስንፍናም ቤት ያፈስሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል። |