ዘዳግም 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብፃውያን ሠራዊት፥ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፥ እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና ጌታ ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጻውያን ሰራዊት፣ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፣ እናንተን ባሳደዷችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና እግዚአብሔር ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ የግብጽን ሠራዊት ከነፈረሶቻቸውና ከነሠረገሎቻቸው በቀይ ባሕር በማስጠም እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ለዘለቄታው እንደ ደመሰሳቸው አይታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተከተሉአችሁም ጊዜ በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ በግብፅ ጭፍራ በፈረሶቻቸውም፥ በሰረገሎቻቸውም ያደረገውን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተከተሉአችሁም ጊዜ በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ በግብፅ ጭፍራ በፈረሶቻቸውም በሰረገሎቻቸውም ያደረገውን፥ |
የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹ ከፈረሰኞቹም ጋር ወደ ባሕር ገቡ፥ ጌታም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ሄዱ።