“እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤
ሐዋርያት ሥራ 8:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፤ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውሃ ወረዱ፤ አጠመቀውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሠረገላውም እንዲቆም አዘዘ። ከዚያም ሁለቱ ዐብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጃንደረባው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወደ ውሃው ወረዱና ፊልጶስ ጃንደረባውን አጠመቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰረገላውንም እንዲያቆሙ አዘዘ፤ አቁመውም ፊልጶስና ጃንደረባው በአንድነት ወደ ውኃው ወረዱ፤ አጠመቀውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም። |
“እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤