ሐዋርያት ሥራ 26:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤’ የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችንም በምድር ላይ ወደቅን፤ እኔም በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ ‘ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን ብትጋፋ ጕዳቱ በአንተ ይብሳል’ የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁላችንም በመሬት ላይ ወድቀን ሳለ በአይሁድ ቋንቋ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? በሰይፍ ስለት ላይ ብትቆም ራስህን ትጐዳለህ’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ፦ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ? በሾለ ብረት ላይ መርገጥ ለአንተ ይብስሃል’ የሚለኝን ቃል ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ “ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል” የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ። |
እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የሚያንገዳግድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ይሁዳ እንደተከበበች ኢየሩሳሌም እንዲሁ ትከበባለች።
በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ በእጁ ወደ ሕዝቡ ጠቀሰ፤ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እየተናገረ እንዲህ አለ።