La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 13:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም አቤሴሎም፥ “እምቢ ካልህ እሽ ወንድሜ አምኖን አብሮን ይሂድ” አለው። ንጉሡም፥ “አብሮህ የሚሄደው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቤሴሎምም፣ “እንግዲያውስ ወንድሜ አምኖን ዐብሮን ይሂድ” አለው። ንጉሡም፣ “ዐብሯችሁ የሚሄደው ስለ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቤሴሎም ግን “መልካም ነው! አንተ መምጣት ካልፈቀድህ ወንድሜ አምኖን እንዲመጣ አትፈቅድለትምን?” ሲል ጠየቀ። ንጉሡም “እርሱስ ቢሆን ለምን ይመጣል?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወን​ድሜ አም​ኖን ከእኛ ጋር እን​ዲ​ሄድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “ከአ​ንተ ጋር ለምን ይሄ​ዳል?” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤሴሎምም አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ አለ። ንጉሡም፦ ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል? አለው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 13:26
8 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም አቤሴሎምን፥ “ልጄ ሆይ፥ ሸክም ስለምናበዛብህ ሁላችንም መሄድ የለብንም” ሲል መለሰለት። አቤሴሎም አጥብቆ ቢለምነውም ንጉሡ መሄድ አልፈለገም፤ ነገር ግን መርቆ አሰናበተው።


ነገር ግን አቤሴሎም አጥብቆ ስለ ለመነው፥ አምኖንና የንጉሡ ወንዶች ልጆች ሁሉ አብረውት እንዲሄዱ አደረገ።


ኢዮአብም አማሳይን፥ “ወንድሜ ሆይ፤ እንደ ምንድንነህ?” አለው፤ ከዚያም አማሳይን የሚስም መስሎ በቀኝ እጁ ጢሙን ያዘው።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።


ወዳጄ ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፥ ኪዳኑንም አፈረሰ።


ጠላት በከንፈሩ ተስፋ ይሰጣል፥ በልቡ ግን ተንኰልን ያኖራል።


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድነው?