2 ነገሥት 4:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንም አውጥታ ለኤልሳዕ በተሠራው ክፍል በማስገባት በአልጋው ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ተመልሳ ሄደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ላይ ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው ዐልጋ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱንም አውጥታ ለኤልሳዕ በተሠራው ክፍል በማስገባት በአልጋው ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ተመልሳ ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውጥታም በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አጋደመችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አጋደመችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች። |
ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አንድ አልጋ፥ አንድ ጠረጴዛ፥ አንድ ወንበርና አንድ የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።”
ባሏንም ጠርታ “አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ዘንድ መሄድ ይገባኛል፤ በተቻለም መጠን ፈጥኜ እመለሳለሁ” አለችው።
እርሷም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት።