ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
1 ተሰሎንቄ 4:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ይህን የማይቀበል፥ የማይቀበለው፥ ሰውን ሳይሆን፥ ቅዱስ መንፈሱን ደግሞም የሰጠንን እግዚአብሔርን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ይህን ምክር ንቆ የማይቀበል፣ የናቀው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይህን ምክር የሚቃወም፥ የሚቃወመው ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የማይቀበል ሰውን ያልተቀበለ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የሚጥል ሰውን የጣለ አይደለም፥ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ። |
ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርክባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
ሙሴም፦ “ጌታ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የሚያጠግባችሁን ምግብ ሲሰጣችሁ ጌታ ያጉረመረማችሁበትን ማጉረምረም ሰምቶ ነው፤ እኛ ምንድን ነን? ማጉረምረማችሁ በጌታ ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይደለም” አለ።
የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፥ ጌታ፥ ሰዎች በሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው፥ ለገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ታማኙ ስለ ጌታ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።’
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
“እናንተ የምትንቁ፥ ተመልከቱ፤ ተደነቁም፤ ጥፉም፤ ማንም ቢተርክላችሁ የማታምኑትን ሥራ በዘመናችሁ እኔ እሠራለሁና፤” ተብሎ በነቢያት የተነገረው እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ።
ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን በነገሯችሁ ነገር፥ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፥ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”