ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ።
1 ሳሙኤል 9:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፥ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጃገረዶቹም “አዎን! እነሆ፥ ሕዝቡ ዛሬ በኮረብታው ላይ መሥዋዕትን ስለሚያቀርብ ባለራእዩ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና ፈጥናችሁ ድረሱበት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቈነጃጅቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊታችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተማዪቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረብታ ላይ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አዎን፥ እነሆ፥ በፊታችሁ ነው፥ ዛሬ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በኮረብታው ላይ ባለው መስገጃ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና ፈጥናችሁ ውጡ። |
ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ።
ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።
ሳሙኤል ግን፥ “ሳኦል ከሰማ ስለሚገድለኝ እንዴት መሄድ እችላለሁ?” አለ። ጌታም እንዲህ አለው፤ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ ‘ለጌታ ልሠዋ መጥቻለሁ’ በል።
የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፤ እንደ ልቤና እንደ ሐሳቤም የሚያደርግ ይሆናል፤ እኔም የጸና ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑንም ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል።
አባትህ ከፈለገኝ፥ ‘ለቤተ ዘመዶቹ ሁሉ ዓመታዊ መሥዋዕት የሚቀርብ ስለሆነ፥ ዳዊት ወደ መኖሪያ ከተማው ወደ ቤተልሔም ቶሎ ለመሄድ አጥብቆ ፈቃድ ጠየቀኝ’ ብለህ ንገረው።