የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤
1 ሳሙኤል 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ወስዳችሁ አንዲት አዲስ ሰረገላ ሥሩ፤ የሚያጠቡም፥ ቀንበር ያልተጫነባቸውን ሁለት ላሞች በሰረገላ ጥመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም ለይታችሁ ወደ ቤት መልሱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ወስዳችሁ አንዲት ሰረገላ ሥሩ፥ የሚያጠቡም፥ ቀን በር ያልተጫነባቸውን ሁለት ላሞች በሰረገላ ጥመዱአቸው፥ እንቦሶቻቸውንም ለይታችሁ ወደ ቤት መልሱአቸው። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤
“ጌታ ያዘዘው የሕጉ ትእዛዝ ይህ ነው፤ መልካሚቱን፥ ነውርም የሌለባትን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ቀይ ጊደር እንዲያመጡልህ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው።