ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤
ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።
እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጕልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤
ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ አንድ ሰው ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አነቃኝ፤
መልአኩም መልሶ፣ “ምን እንደ ሆኑ አታውቅምን?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።
ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደ ሆነ እይ” አለኝ።