Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘካርያስ 2:2

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው፤” አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መለኪያ ገመዱም ከዚያ ጀምሮ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኰረብታ፣ ዐልፎም ወደ ጎዓ ይዘረጋል።

ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።

“ ‘ከተቀደሰው ስፍራ ጋራ የተያያዘ ወርዱ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ የሆነ ቦታ ለከተማዪቱ ርስት አድርገህ ስጥ፤ ይህም ለመላው የእስራኤል ቤት ይሆናል።

“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በምሕረት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ፤ በዚያም ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረውንም መልአክ፣ “ቅርጫቱን የሚወስዱት ወዴት ነው?” አልሁት።

“እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ከዚያም ሸንበቆ የመሰለ መለኪያ በትር ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ፤ “ሄደህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና መሠዊያውን ለካ፤ በዚያም የሚያመልኩትን ቍጠር።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች