ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤ የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።
“የእኔስ ቤት በአምላክ ዘንድ ትክክል አይደለምን? ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ ከእኔ ጋራ ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን? ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?
ምሰሶዎቹን ከብር፣ መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ፍቅር የተለበጠ ነው።
እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤
ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤ የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣ እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።
ከዚያም ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበርር አየሁ፤ እርሱም በምድር ላይ ለሚኖሩ ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ የሚሰብከውን የዘላለም ወንጌል ይዞ ነበር፤