ሁሉም ሰይፍ የታጠቁ፣ ሁሉም በጦርነት የተፈተኑ ናቸው፤ የሌሊት አደጋን ለመከላከልም፣ እያንዳንዳቸው ሰይፋቸውን በወገባቸው ታጥቀዋል።
ከዚያ ቀን ጀምሮ ከሰዎቼ እኩሌቶቹ ሥራውን ሠሩ፤ የቀሩት ደግሞ ጋሻና ጦር፣ ቀስትና ጥሩር ይዘው ነበር። የጦር አለቆች ከመላው የይሁዳ ሕዝብ በስተኋላ ቆሙ፤
እነርሱም ቅጥሩን ይገነቡ ነበር፤ ዕቃ የሚሸከሙት በአንድ እጃቸው ሥራቸውን ሲሠሩ፣ በሌላው እጃቸው የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ነበር፤
ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ።
የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤
እነሆ፤ የሰሎሞን ሠረገላ በታዋቂዎቹ የእስራኤል መኳንንት፣ ስድሳ ጦረኞች ታጅባለች፤
ንጉሥ ሰሎሞን የራሱን ሠረገላ ሠራ፤ የሠራውም ከሊባኖስ በመጣ ዕንጨት ነው።
እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ዘወትር ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ስለዚህ ማንም አይጐዳውም፣ ቀንና ሌሊት እጠብቀዋለሁ፤
የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።
እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው።