ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።
አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህ! እንዴትስ ታምራለህ! ዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
ውዴ ሆይ፤ የፈርዖንን ሠረገሎች ከሚስቡ ፈረሶች መካከል፣ በአንዲቱ ባዝራ መሰልሁሽ።
ውዴም እንዲህ አለኝ፤ “ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺ፤ አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋራ ነዪ።
በለስ ፍሬዋን አፈራች፤ ያበቡ ወይኖችም መዐዛቸውን ሰጡ፤ ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺና ነዪ፤ አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋራ ነዪ።”
ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ! ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጕርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው።
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ የሚያረካ ነው፤ የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!
ውዴ ሆይ፤ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ እንከንም አይወጣልሽም።
ዐይኖቹ፣ በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣ በወተት የታጠቡ፣ እንደ ዕንቍም ጕብ ጕብ ያሉ ናቸው።
እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”
እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣ እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?
ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣ እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ የምትይ ነሽ! ፍቅሬ ሆይ፤ የምታስደስቺ ነሽ።
ቁመናሽ እንደ ዘንባባ ዛፍ መለል ያለ ነው፤ ጡቶችሽም የፍሬውን ዘለላ ይመስላሉ።
እናንተም፣ “ለምን ይህ ሆነ?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ። ይህ የሆነው የትዳር ጓደኛህን፣ አጋርህንና የቃል ኪዳን ሚስትህን አታልለሃታልና፣ እግዚአብሔር በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምስክር ስለ ሆነ ነው።