ውዴ ለእኔ ከዓይንጋዲ የወይን ተክል ቦታ እንደ መጣ የሄና አበባ ዕቅፍ ነው።
ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንዳረፈ፣ በመቋጠሪያ እንዳለ ከርቤ ነው።
በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኮይ፣ ውዴም በጕልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤ በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤ የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።
ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዓይንጋዲ ምሽጎች ተቀመጠ።