እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ።
አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
የቍጣህ ክብደት በላዬ ዐርፏል፤ በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ
በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤ የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣ በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።
ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤ ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣ በቍጣህ አትምጣብኝ።
እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤ በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።’
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዝናህን ሰምቻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህም አስፈራኝ፤ በእኛ ዘመን አድሳቸው፤ በእኛም ጊዜ እንዲታወቁ አድርግ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን ዐስብ።
እናንተን ሊያጠፋችሁ ክፉኛ ተቈጥቶ ነበርና፣ እኔም የእግዚአብሔርን ቍጣና መዓት ፈራሁ፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ገና ሰማኝ።