ግብጽ ሆይ፤ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽ ታምራትንና ድንቅን ሰደደ።
ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብጻውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ።
ፈርዖንንና ሰራዊቱን በቀይ ባሕር ያሰጠመ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
አባቶቻቸው በዐይናቸው እያዩ፣ በግብጽ አገር፣ በጣኔዎስ ምድር ታምራት አደረገ።
እርሱም መርቶ ከግብጽ አወጣቸው፤ በግብጽ፣ በቀይ ባሕርና በምድረ በዳ አርባ ዓመት ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን አደረገ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር በዐይናችሁ እያያችሁ ለእናንተ በግብጽ እንዳደረገው ሁሉ በፈተና፣ በታምራዊ ምልክቶችና በድንቆች፣ በጦርነት፣ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ወይም በታላቅና በአስፈሪ ሥራዎች ከሌላ ሕዝብ መካከል አንድን ሕዝብ የራሱ ለማድረግ የቻለ አምላክ አለን?
እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብጽ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።