ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።
ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፏቸው፤ ምድሩንም ወረሱ።