ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።
በዚህ ጊዜ ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።
በሰጠሃቸውም ጊዜ፣ አንድ ላይ ያከማቻሉ፤ እጅህንም ስትዘረጋ፣ በመልካም ነገር ይጠግባሉ።
እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቷልና፤ የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቧል።
ጠላቶቼ እያዩ፣ በፊቴ ማእድ አዘጋጀህልኝ፤ ራሴን በዘይት ቀባህ፤ ጽዋዬም ሞልቶ ይፈስሳል።
ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
ብፁዕ ነው፤ አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣ በአደባባይህም ያኖርኸው፤ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንረካለን።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብጽ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።
ስለዚህ ተስፋ አንቈርጥም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየጠፋ ቢሄድም እንኳ፣ ውስጣዊው ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፤
በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ሙሴ በላከኝ ጊዜ የነበረኝ ብርታት ዛሬም ዐብሮኝ አለ፤ ልክ እንደዚያን ጊዜ ሁሉ አሁንም ወደ ጦርነት ለመሄድ፣ ለመውጣትም ለመግባትም ኀይሉም ብርታቱም አለኝ።