ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣
ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣ መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።
መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤ የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።
እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤ እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤ በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።
በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለስ ዘንድ፣ ነፍሴን ከሞት፣ እግሬንም ከመሰናክል አድነሃልና።
ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።
ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው።
እነሆ፤ በሥቃይ የተጨነቅሁት፣ ለጥቅሜ ሆነ፤ ከጥፋት ጕድጓድ፣ በፍቅርህ ጠበቅኸኝ፤ ኀጢአቴንም ሁሉ፣ ወደ ኋላህ ጣልህ።
ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣ እራራልሻለሁ” ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
በፈተና የሚጸና ሰው ብፁዕ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወድዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል።
የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን አክሊል ትቀበላላችሁ።
እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።