በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን? ከርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።
ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።
ዕውቀት አልባ የሆነ ቀናኢነት መልካም አይደለም፤ ጥድፊያም መንገድን ያስታል።
የትጉህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።
ራሱን እንደ ጠቢብ የሚቈጥረውን ሰው አይተሃልን? ከርሱ ይልቅ ለሞኝ ተስፋ አለው።
ሞኝ ሰው ቍጣውን ያለ ገደብ ይለቅቀዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።
አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።
ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣ የኋላ ኋላ ሐዘን ያገኘዋል።
በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤