አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።
አገልጋዬን ብጣራ፣ በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም።
ለፈረስ ዐለንጋ፣ ለአህያ መሸበቢያ፣ ለሞኝ ጀርባም በትር ይገባዋል።
ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።
በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን? ከርሱ ይልቅ ሞኝ ተስፋ አለው።
ባሪያ ሲነግሥ፣ ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፣