ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል።
መልእክተኞቹ በንጉሡ ትእዛዝ ተቻኵለው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተላለፈ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፤ የሱሳ ከተማ ግን ግራ ተጋብታ ነበር።
መርዶክዮስ ሰማያዊና ነጭ የቤተ መንግሥት ልብስ ለብሶ፣ ትልቅ የወርቅ አክሊል ደፍቶ፣ ከቀጭን በፍታና ከሐምራዊ ግምጃ የተሠራ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ ከንጉሡ ፊት ወጣ፤ የሱሳ ከተማም ደስታ የተሞላበት በዓል አከበረች።
ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሰው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።
ጻድቃን ሲሳካላቸው ከተማ ደስ ይላታል፤ ክፉዎች ሲጠፉ እልልታ ይሆናል።
ጻድቃን ድል ሲነሡ ታላቅ ደስታ ይሆናል፤ ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሕዝብ ይሸሸጋል።
ታዳጊ በሌለው ሕዝብ ላይ የተሾመ ጨካኝ ገዥ፣ እንደሚያገሣ አንበሳ ወይም ተንደርድሮ እንደሚይዝ ድብ ነው።
ክፉዎች ሥልጣን በሚይዙ ጊዜ ሕዝብ ይሸሸጋል፤ ክፉዎች በሚጠፉበት ጊዜ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
ከፀሓይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፤ ይህም ከገዥ የሚወጣ ስሕተት ነው፤
ሞኞች በብዙ የክብር ስፍራዎች ሲቀመጡ፣ ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ስፍራ ሆነዋል።
እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤ የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም።
ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ።
ንጉሡ ሄሮድስ ይህን በሰማ ጊዜ ታወከ፤ እንዲሁም መላዪቱ ኢየሩሳሌም ዐብራ ታወከች።
ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፤ “የዓለም መንግሥት፣ የጌታችንና የርሱ ክርስቶስ መንግሥት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”