ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።
ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ ጸሎቱም ለፍርድ ትሁንበት።
ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።
ዐመፃን ሕጋዊ የሚያደርግ፣ የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋራ ሊያብር ይችላልን?
እግዚአብሔር ጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤ የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።
እግዚአብሔር የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሠኘዋል።
ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣ እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።
የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!
እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው።
ቢጾሙም ጩኸታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ቢያቀርቡም አልቀበላቸውም፤ ነገር ግን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር አጠፋቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር የሚሰማው፣ የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እንጂ፣ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤