በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።
እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ባለማዘኑም ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት።”
ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ድኾችንም ከሞት ያድናል።
“ከሕዝቤ መካከል ችግረኛ ለሆነው ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ ዐራጣ አበዳሪ አትሁኑ፤ ወለድ አትጠይቁት።
ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።
ጎረቤቱን የሚንቅ ኀጢአት ይሠራል፤ ለተቸገሩት የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።
ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።
ድኻ በሥጋ ዘመዶቹ ሁሉ የተጠላ ነው፤ ታዲያ ወዳጆቹማ የቱን ያህል ይሸሹት! እየተከታተለ ቢለማመጣቸውም፣ ከቶ አያገኛቸውም።
አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
በዐራጣ ቢያበድር፤ ከፍተኛ ወለድም ቢቀበል፣ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ይኖራልን? ከቶ አይኖርም! እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች አድርጓልና በርግጥ ይሞታል፤ ደሙም በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል።
እጁን ደኻን ከመበደል ቢሰበስብ፣ ዐራጣ ወይም ከፍተኛ ወለድ ባይቀበል፣ ሕጌን ቢጠብቅ፣ ሥርዐቴንም ቢከተል፣ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኀጢአት አይሞትም።
በዐራጣ አያበድርም፣ ከፍተኛ ወለድም አይቀበልም። እጁን ከበደል ይሰበስባል፤ በሰውና በሰው መካከል በትክክል ይፈርዳል።
ወገንህ በመካከልህ ይኖር ዘንድ ምንም ዐይነት ወለድ አትቀበለው፤ አምላክህን ፍራው።