በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤ የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።
ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስን ያመጣል።
ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣ እውነተኛና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን?
ከሩቅ የሚመጣ መልካም ዜና፣ የተጠማችን ነፍስ እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውሃ ነው።
በሞኝ እጅ መልእክትን መላክ፣ የገዛ እግርን እንደ መቍረጥ ወይም መርዝ እንደ መጋት ነው።
ከዚያም የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ፣ ከሮቤልና ከጋድ ወገኖች ጋራ በገለዓድ ምድር ከተነጋገሩ በኋላ፣ ወደ ከነዓን ተመልሰው፣ ሁኔታውን ለእስራኤላውያን ነገሩ።