የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣ እንደ ወርቅ ጕትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።
“እናንተ የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፣ ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፣ ለሳኦል አልቅሱለት።
ወርቅም ብርሌም አይወዳደሯትም፤ በወርቅ ጌጥም አትለወጥም።
ወንድሞቹና እኅቶቹ፣ ቀድሞም ያውቁት የነበሩ ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ በቤቱም ከርሱ ጋራ ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘናቸውን ገለጡለት፤ እግዚአብሔርም ካመጣበት መከራ ሁሉ አጽናኑት፤ እያንዳንዳቸውም ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።
አሮንም፣ “የሚስቶቻችሁን፣ የወንድና የሴት ልጆቻችሁን የጆሮ ወርቅ አውልቃችሁ ወደ እኔ አምጡ” ብሎ መለሰላቸው።
ፈቃደኛ የነበሩ ሁሉ፣ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው ከሁሉም ዐይነት የወርቅ ጌጦች አመጡ፤ የአፍንጫ ጌጦችን፣ ሎቲዎችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ጌጣጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሁሉም ወርቃቸውን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
ቂል የአባቱን ምክር ይንቃል፤ መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል።
የሚሰሙ ጆሮዎች፣ የሚያዩ ዐይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሠርቷቸዋል።
ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድድሃል።
የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣ የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል።
በአፍንጫሽ ቀለበት፣ በጆሮሽ ጕትቻ፣ በራስሽም ላይ ውብ አክሊል አደረግሁልሽ፤
መልካም ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር መልካም ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ካከማቸው ክፉ ነገር መጥፎ ነገርን ያወጣል።