አንተም፣ “መቱኝ፤ አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ፤ አልተሰማኝም፤ ታዲያ፣ ሌላ መጠጥ እንዳገኝ፣ መቼ ነው የምነቃው?” ትላለህ።
በባሕር ላይ የተኛህ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ የተጋደምህ ትመስላለህ።
ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣ ሞኝም ቂልነቱን ይደጋግማል።
ቂልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣ እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቅቀው፣ ቂልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።
ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ! “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ።
እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።
“የኤፍሬምን የሲቃ እንጕርጕሮ በርግጥ ሰምቻለሁ፤ ‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤ እኔም ተቀጣሁ። አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣ መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።
ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።
እንዲህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፣ በልቡ ራሱን በመባረክ፣ “እንደ ልቤ ሐሳብ ብኖርም እንኳ ሰላም አለኝ” ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።
“ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል” እንዲሁም “ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።