በባሕር ላይ የተኛህ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ የተጋደምህ ትመስላለህ።
አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፣ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ ከዚያም እኔ አምኖንን፣ ‘ምቱት’ ስላችሁ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝ አትፍሩ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” ብሎ አዘዛቸው።
ከሹማምቱ አንዱና የግማሽ ሠረገሎቹ አዛዥ የሆነው ዘምሪ ዐምፆ ተነሣበት፤ በዚያ ጊዜ ኤላ በቴርሳ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው በአርጻ ቤት ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፤
በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ ውሆች ተቈለሉ፤ ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።
ዐይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ አእምሮህም ይቀባዥራል።
አንተም፣ “መቱኝ፤ አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ፤ አልተሰማኝም፤ ታዲያ፣ ሌላ መጠጥ እንዳገኝ፣ መቼ ነው የምነቃው?” ትላለህ።
“ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤
እናንተ ሰካራሞች፤ ተነሡ፤ አልቅሱ፤ እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ሁሉ፤ ዋይ በሉ፤ ስለ አዲሱ የወይን ጠጅ ዋይ ብላችሁ አልቅሱ፤ አፋችሁ ላይ እንዳለ ተነጥቃችኋልና።
ከጥፋት ውሃ በፊት ኖኅ ወደ መርከቡ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደ ነበሩ፣
“እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤