Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ምሳሌ 17:26

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”

በል አሁን ተነሥተህ ውጣና ሰዎችህን አበረታታ፤ ባትወጣ ግን በዚች ሌሊት አንድም ሰው ዐብሮህ እንደማይሆን በእግዚአብሔር እምላለሁ፤ ይህ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ክፉ ነገር ሁሉ የባሰ መከራ ያስከትልብሃል።”

ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፣ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”

በደለኛውን ማጽደቅ ሆነ፣ ጻድቁን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።

ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል።

ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት ጠባቂዎች አንዱ፣ “ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው እንዲህ ነውን?” ብሎ በጥፊ መታው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች