ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።
ለኢዮአብ፣ “ንጉሡ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አቤሴሎም እያለቀሰ እያዘነ ነው” ተብሎ ተነገረው።
የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል።
ሞኝ ልጅ መውለድ ሐዘን ያስከትላል፤ የተላላም አባት ደስታ የለውም።
ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት።
አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።
የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።