ከብንያም ነገድ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፤
“ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።”
የሚመራቸው ትንሹ ብንያም ነው፤ በዚያ በብዙ የሚቈጠሩ የይሁዳ መሳፍንት፣ እንዲሁም የዛብሎንና የንፍታሌም መሳፍንት ይገኛሉ።
የዳን ነገድ መሪ፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፤
ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በርሱ ተጠብቆ ያለ ሥጋት ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወድደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”