ከዲቦንጋድ ተነሥተው በዓልሞን ዲብላታይም ሰፈሩ።
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
“ሞዓብን የሚያጠፋ፣ በአንቺ ላይ ይመጣልና፤ የተመሸጉ ከተሞችሽንም ያጠፋልና፤ አንቺ የዲቦን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከክብርሽ ውረጂ፤ በደረቅም መሬት ተቀመጪ።
በዲቦን፣ በናባውና በቤትዲብላታይም ላይ፣
እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ የሚኖሩበትንም ስፍራ ከምድረ በዳው እስከ ዴብላታ ድረስ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፤ ያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ።
የጋድ ልጆች፤ ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣
ከጋይም ተነሥተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ።
ከዓልሞን ዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ።