ለጦርነት ዝግጁ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ እዚሁ ይሆናል።”
“ርስት አድርጌ ወደምሰጣቸው ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፣ በዚያ አገር አንዱን ቤት በተላላፊ በሽታ የበከልሁ እንደ ሆነ፣
ድርሻችንን ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ስላገኘን፣ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእነርሱ ጋራ የምንካፈለው አንዳችም ርስት አይኖርም።”
የጋድና የሮቤል ሰዎች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ባሪያዎችህ እግዚአብሔር ያለውን ያደርጋሉ፤
ከዚያም ሙሴ፣ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛትና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ግዛት፣ ማለትም ምድሪቱንና ከነከተሞቿ በዙሪያዋ ያለውን ግዛት በሙሉ ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጣቸው።
እነዚህ ሁለቱ ነገዶችና እኩሌታው ነገድ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ፣ ከኢያሪኮ ማዶ በፀሓይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።”
ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ዓረባ በተባለው ምድረ በዳ ከሱጵ ትይዩ፣ በፋራንና በጦፌል፣ በላባን፣ በሐጼሮትና በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፣ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን።
በዚያ ጊዜ ከያዝነው ምድር ላይ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ በስተሰሜን ያለውን ግዛት፣ በተጨማሪም ኰረብታማውን የገለዓድ አገር እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።
እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።