የጋድና የሮቤል ሰዎች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ባሪያዎችህ እግዚአብሔር ያለውን ያደርጋሉ፤
ለጦርነት ተዘጋጅተው ከእናንተ ጋራ ካልተሻገሩ ግን፣ ርስታቸውን ዐብረዋችሁ በከነዓን መካፈል አለባቸው።”
ለጦርነት ዝግጁ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ እዚሁ ይሆናል።”
“ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤ የወገኖቹ ቍጥርም አይጕደልበት።”
እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን።