አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተቈጠሩት ወንዶች ሁሉ ብዛታቸው ስድስት ሺሕ ሁለት መቶ ነበር።
ከሮቤል ነገድ የተቈጠሩት አርባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነው።
በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺሕ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።
የሞሖላውያንና የሙሳያውያን ጐሣዎች ከሜራሪ ወገን ናቸው፤ እነዚህም የሜራሪ ጐሣዎች ነበሩ።
የሜራሪም ጐሣዎች ቤተ ሰቦች አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ይሆናል፤ የሜራሪም ጐሣዎች ከማደሪያው ድንኳን በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ።