የሞሖላውያንና የሙሳያውያን ጐሣዎች ከሜራሪ ወገን ናቸው፤ እነዚህም የሜራሪ ጐሣዎች ነበሩ።
የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ። የሞሖሊ ወንዶች ልጆች፤ አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።
የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤ የሊብናውያን ጐሣ፣ የኬብሮናውያን ጐሣ፣ የሞሖላውያን ጐሣ፣ የሙሳውያን ጐሣ፣ የቆሬያውያን ጐሣ። ቀዓት የእንበረም አባት ነበረ፤
የሜራሪ ጐሣዎች፤ ሞሖሊና ሙሲ። እንግዲህ የሌዋውያን ጐሣዎች በየቤተ ሰባቸው ሲቈጠሩ እነዚህ ናቸው።
ዋናው የሌዋውያን አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነው፤ እርሱም መቅደሱን ለመጠበቅ ኀላፊ በሆኑት ላይ ተሹሞ ነበር።
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተቈጠሩት ወንዶች ሁሉ ብዛታቸው ስድስት ሺሕ ሁለት መቶ ነበር።
“ሜራሪያውያንን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰቦቻቸው ቍጠራቸው፤