እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።
የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤
የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣ በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣ በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣