የሱቱላ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጐሣ፤
የኤፍሬም ዘሮች፤ ሱቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ ልጁ ታሐት፣
የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣ በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤
እነዚህ የኤፍሬም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ። እነዚህም በየጐሣቸው የተቈጠሩ የዮሴፍ ዘሮች ነበሩ።