Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ነህምያ 4:4

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላካችን ሆይ፤ ተንቀናልና ስማን፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ አውርድባቸው፤ በምርኮ ምድር እንዲበዘበዙ አሳልፈህ ስጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ በመቀጠል እንዲህ አልሁ፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ትክክል አይደለም፤ የጠላቶቻችንን የአሕዛብን ስድብ ለማስወገድ የአምላካችንን መንገድ በፍርሀት መከተል አይገባችሁምን?

ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።

እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።

“ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግህብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቷል፤ ልቤም ደክሟል።”

ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፣ “ለመሆኑ ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች